ጀማል ጣሰው ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል

አንጋፋው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው በአዲሱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጥሪ ደርሶታል፡፡

ከአስር ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በርካታ ጨዋታዎችን ተሰልፎ የተጫወተው የቀድሞው ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መከላከያ፣ ጅማ አባቡና እና ድሬዳዋ ከተማ ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው ከ2011 ጀምሮ ደግሞ በፋሲል ከነማ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን በተለይ በተሰረዘው የውድድር ዓመት በዐፄዎቹ ቤት በርካታ ጨዋታዎችን ባያደርግም በዋልያዎቹ ስብስብ ተካቷል፡፡ በ2011 መጨረሻ ከሌሶቶ ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ በድጋሚ ጥሪ የደረሰው ጀማል ከአርባዎቹ ተጫዋቾች ጋር አብሮ ያልተጠራበት ምክንያት ባይታወቅም የጊዜያዊ ስብስቡ አርባ አንደኛ፤ እንዲሁም ስድስተኛው ግብ ጠባቂ ሆኗል፡፡

ከዚህ በኃላም ለሌሎች ተጫዋቾች ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን ሦስት ጥሪ የደረሳቸው ተጫዋቾች ቡድኑን ላይቀላቀሉ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ ባደረግነው ማጣራት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: