የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ፀኃፊ የሀድያ ሆሳዕና ረዳት አሰልጣኝ ሆኑ

ዶክተር ኢያሱ መርሐፅድቅ የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ረዳት በመሆን ተሹመዋል፡፡

ዶ/ር ኢያሱ በ1990ዎቹ አጋማሽ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውስጥ በቴክኒክ ኮሚቴ አባልነት እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ ክለብ በአማካሪነት የሰሩ ሲሆን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲም በመምህርነት እና የስፖርት ዲን በመሆን ከሰሩ በኃላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመስራት አሳልፈዋል። አሁን ደግሞ ወደ አሰልጣኝነቱ ብቅ በማለት በዛሬው ዕለት የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ረዳት በመሆን ተቀጥረዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: