ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችን ውል አድሷል

ድሬዳዋ ከተማዎች በዛሬው ዕለት አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራትም አራዝመዋል፡፡

የዋና አሰልጣኟን ብዙዓየሁ ጀምበሩን ውል በማራዘም ረዳት አሰልጣኝ ከመደቡ በኃላ ከአንድ ሳምንት በፊት የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት ያራዘሙት ድሬዳዋ ከተማዎች በዛሬው ዕለት አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የስድስት ወሳኝ የቡድኑ አባላትን ኮንትራት አድሷል፡፡

ሀዋሳ ከተማን ለቃ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በአዲስ አዳጊው አቃቂ ቃሊቲ ስትጫወት የነበረችው አማካይዋ ብርቄ አማረ፣ በተመሳሳይ በሀዋሳ ከተማ በመጫወት አሳልፋ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ስትጫወት የነበረችው አጥቂዋ አሥራት ዓለሙ፣ ወጣቷ የአርባ ምንጭ ከተማ ግብ ጠባቂ አበባየሁ ጣሰው እና ሀዋሳ ከተማን ለቃ ወደ ቀድሞ ክለቧ አርባ ምንጭ ተመልሳ ቡድኑን በአምበልነት እና በአማካይ ተጫዋችነት ስታገለግል የቋየችው ትሁን አየለ አዲሶቹ የብርቱካናማዎቹ ፈራሚዎች ሆነዋል፡፡

አሰልጣኝ ብዙአየው ጀምበሩ ለሶከር ኢትዮጵያ እንገለፀችው የክለቡ ወሳኝ ተጫዋቾች የሆኑት አምበሏ ብዙሀን እንዳለ፣ ተከላካዮቹ ማኅደር ባዬ እና ሀሳቤ ሙሶን ጨምሮ ማዕድን ሳዕሉ፣ ፀሐይነሽ በቀለ እና ታደለች አብርሀም ለተጨማሪ አንድ እና ሁለት ዓመት ለመቆየት ፊርማቸውን ያኖሩ ነባር ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!