የኢትዮጵያ ቀጣይ ተጋጣሚ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ልታደርግ ነው

ኒጀሮች ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል።

በጥቅምት ወር መጨረሻ እና ኅዳር ወር መጀመርያ በተከታታይ የምድብ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚገጥሙት ኒጀሮች ከቀናት በፊት ፈረንሳዊው ዣን ሚሼል ካቫሊን አሰልጣኝ አድርገው መቅጠራቸው የሚታወስ ሲሆን ለኢትዮጵያ ጨዋታ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ ከቻድ እና ሴራልዮን ጋር የአቋም መለክያ ጨዋታዎች ለማድረግ ቀጠሮ ይዘዋል። በቀጣይ ቀናት ይፋዊ የፊርማ ሥነ-ስርዓት ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት አዲሱ አሰልጣኝ ለሁለቱም የአቋም መለክያ ጨዋታዎች የሚጠቀሙባቸው ተጫዋቾችንም ይፋ አድርገዋል።

ኒጀሮች በማጣርያ ጨዋታዎቹ ማዳጋስካር እና አይቮሪኮስትን ገጥመው በሁለቱም ጨዋታዎች ሽንፈት ገጥሟቸው ያለምንም ነጥብ በአምስት የግብ ዕዳ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!