የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በኅዳር ወር አጋማሽ ይጀመራል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴቶች ፕሪምየር ሊግ በኅዳር ወር አጋማሽ እንደሚጀመር ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀመሩ ከሳምንት በፊት ከመንግሥት ፍቃድ በማግኘቱ በየደረጃው ያሉ የሊግ ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀመሩ ቅድመ ሥራዎች እየተከወኑ ይገኛሉ፡፡ በፌዴሬሽኑ ከሚዘጋጁ ውድድሮች መካከል የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ እና ሁለተኛ ዱቪዚዮን የሚጠቀሱ ሲሆን እነዚህን የሊግ መርሀ ግብሮች በ2013 እንዲካሄዱ የማስጀመሪያ ወሩን በመግለፅ ክለቦች ዝግጅት እንዲያየርጉ ዛሬ ደብዳቤን ለክለቦቹ መላኩን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ክለቦች የጤና ሚኒስቴርም ሆነ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያወጡትን የኮቪድ መከላከያ ቅድመ መመሪያ ወይንም ፕሮቶኮልን ተግባራዊ በማድረግ ወደ ልምምድ መመለስ እንደሚችሉ በደብዳቤው ገልፆ በኅዳር ወር አጋማሽ ደግሞ ውድድሮቹ በድጋሚ የሚጀመሩበት ወቅት መሆኑን ጠቅሶ መላኩን ሰምተናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!