ወላይታ ድቻ አጥቂ አስፈረመ

የጦና ንቦቹ ወጣቱ አጥቂ ያሬድ ዳርዛን አስፈረሙ፡፡

ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኃላ ለክለቡ ዋናው ቡድን ሳይጫወት ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በከፍተኛ ሊጉ ለርባምንጭ ከተማ እና ኢኮሥኮ አምርቶ በመጫወት ያሳለፈው የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ያሬድ የዝውውር መስኮቱ ከመከፈቱ በፊት ቅድመ ስምምነት ከፈፀሙ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን ወደ ልጅነት ቡድኑ የሚመልሰውን የሁለት ዓመት ኮንትራት በመፈራረም በዛሬው ዕለት ቡድኑን ተቀላቅሏል፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ በመከላከያ ውል እያለው ወደ ወላይታ ድቻ በማምራቱ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ የነበረው የቀኝ መስመር ተከላካዩ አናጋው ባደግ ከመከላከያ ጋር በስምምነት በመለያየት ለድቻ መፈረሙ ተሰምቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!