ስሑል ሽረ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ባለፈው ሳምንት ወደ ዝውውር የገባው ስሑል ሽረ ሁለት ተጫዋች አስፈርሟል፡፡

ደሳለኝ ደባሽ ወደ ቀድም ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል፡፡ ይህ የቀድሞ የአዳማ ከተማ የአማካይ እና የተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ስሑል ሽረን ከለቀቀ በኃላ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በሰበታ ከተማ አሳልፎ በድጋሚ ወደ ስሑል ሽረ ተመልሶ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ሌላኛው የክለቡ ፈራሚ አጥቂው ዘካሪያስ ፍቅሬ ነው፡፡ ይህ የቀድሞው ሀላባ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ አርባምንጭ ከተማ እና ዓምና ደግሞ የከፍተኛ ሊጉ አክሱም ከተማን ተቀላቅሎ የተጫወተው አጥቂ ከሁለት ዓመታት በኃላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሶ ስሑል ሽረን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: