ከፍተኛ ሊግ | መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ መከላከያ ሁለት ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ግብ ጠባቂው ምህረትአብ ገብረህይወት የመከላከያ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በመቐለ 70 እንደርታ ያለፉትን ዓመታት ሲጫወት የነበረው ይህ የቀድሞ የደደቢት ግብ ጠባቂ በአመዛኙ በክለቡ ውስጥ ተጠባባቂ በመሆን ያሳለፈ ሲሆን በቅርቡ ለጦሩ ከፈረመው ጃፈር ደሊል ጋር ተፎካካሪ ለመሆን ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡

ሌላው የክለቡ ፈራሚ ታሪኩ እሸቱ ነው፡፡ ይህ የግራ መስመር ወጣት ተከላካይ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭን ለቆ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት ለከፍተኛ ሊጉ ገላን ከተማ በመጫወት ካሳለፈ በኃላ ለዘንድሮው ዓመት ለመከላከያ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመሩት መከላከያዎች በዛሬው ዕለት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን አመሻሹን በደብረዘይት ይጀምራሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: