ከፍተኛ ሊግ | መከላከያ ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን አስፈረመ

እስካሁን አምስት ተጫዋቾችን ያስፈረሙት መከላከያዎች ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን ጨምረዋል፡፡

አጥቂው ፍቃዱ ወርቁ ለአንድ ዓመት ጦሩን የተቀላቀለ ተጫዋች ሆኗል፡፡ የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች ያለፉትን ሦስት የውድድር ዓመታት በባህር ዳር ከተማ ሲጫወት አሳልፏል።

ሌላኛው ፈራሚ የጅቡቲ ዜግነት ያለው የመስመር እና የፊት አጥቂው አብዲ መሀመድ ነው፡፡ ይህ ወጣት ተጫዋች ከዚህ ቀደም ለድሬዳዋ ከተማ ሲጫወት የቆየ ሲሆን ከ2010 ጀምሮ ደግሞ ወደ ጅቡቲ አምርቶ በሀገሪቱ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ሲጫወት ቆይቶ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለመከላከያ ፈርሟል፡፡ ተጫዋቹ ከወራቶች በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጅቡቲን በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ እየተመራች ስትጫወት ለጅቡቲ ተሰልፎ በመጫወት መልካም እንቅስቃሴን ማሳየቱ ይታወሳል፡፡

ሌላኛው የመከላከያ ፈራሚ የመሀል እና የመስመር ተከላካዩ ዮሐንስ ዘገዬ ነው፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ተጫውቶ በመቀጠል ለኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ በ2012 የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ደቡብ ፖሊስ ቆይታን ካደረገ በኃላ ለዘንድሮው የውድድር አመት የጦሩ ስምንተኛ ፈራሚ ሆኗል፡፡

ዘጠነኛው የክለቡ ፈራሚ በኢትዮጵያ መድን በተከላካይ ቦታ ላይ ሲጫወት የነበረው ኢብራሂም ሁሴን ነው፡፡

መከላከያ ከአዳዲስ ፈራሚዎቹ ባሻገር የነባሮቹን፡ አቤል ነጋሽ፣ በኃይሉ ግርማ እና ዳዊት ወርቁን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!