ባህር ዳር ላይ የሚደረገውን ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል

ኢትዮጵያ ኒጀርን የምታስተናግድበት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አራተኛ የምድብ ጨዋታ የሚመሩ ዳኞችን ካፍ አሳውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የ2021 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛ ጨዋታዋን ኒያሜ ላይ ኅዳር አራት የምታደርግ ሲሆን በድጋሚ ከኒጀር ጋር አራተኛውን ጨዋታ ከአራት ቀናት በኃላ ማለትም ኅዳር ስምንት በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ታከናውናለች፡፡ ይህን የማጣሪያ ጨዋታ ደግሞ አራት የሴራሊዮን ዜግነት ያላቸው ዳኞች ይመሩታል፡፡ ዳዱ ዊሊያምስ በመሐል ዳኝነት ሲመደብ አሊዩ ሳዲ ሙሳ እና ኢብራሂም ባህ ደግሞ የዳዱ ረዳት ዳኞች ሆነዋል፡፡ ራይሞንድ አዴይሚ አራተኛ ዳኛ ሲሆን ደቡብ አፍሪካዊው ሲንፒዊ ብሪያን በታዛቢ ኮሚሽነርነት በካፍ መመረጣቸው ተገልጿል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!