የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንታት ጨዋታዎች የሚደረጉበት ሜዳ ተወስኗል

ታኅሣሥ 3 እንደሚጀመር የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት ሳምንታት ጨዋታዎች የት እንደሚደረጉ ከውሳኔ ተደርሷል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮቪድ 19 የመከላከል ሒደትን በመከተል የሚደረግ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙ ሳይሆን በተመረጡ ስታዲየሞች ላይ ብቻ እንደሚካሄድም ይታወቃል። የሊግ ኩባንያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ፕሪምየር ሊጉ ታኀሣሥ 3 ሲጀመር የመጀመሪያዎቹ አምስት ሳምንታት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደረጉ መወሰኑን ገልፀውልናል፡፡ አቶ ክፍሌ በገለፃቸው “ከዲኤስቲቪ ጋር ተነጋግረን ነበር የመጀመሪያ አምስት ሳምንታት 40 ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲሆን ወስነናል። በቀጣይ ቀሪዎቹን አምስት ሜዳዎች እና የሚደረጉትን ጨዋታዎች እንገልፃለን።” በማለት ተናግረዋል፡፡

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርአት በቀጣይ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ እንደሚወጣ የተሰማ ሲሆን የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ለመስጠትም ትናንት ምሽት የዲኤስ ቲቪ ባለሙያዎች አዲስ አበባ እንደገቡ አቶ ክፍሌ አክለው ነግረውናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!