ኢትዮጵያ ቡና ከ ኤሌክትሪክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና 1-0 ኤሌክትሪክ
58′ ጋቶች ፓኖም (ፍቅም)

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ይህ ውጤት ለቡና 4ኛ ተከታታይ ድል ፣ ለኤሌክትሪክ 4ኛ ተከታታይ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ቢጫ ካርድ
90+2′
ሄሱ ሀሪሰን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
85′
መስኡድ መሀመድ ወጥቶ ሳላምላክ ተገኝ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
84′
ጋቶች ፓኖም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
83′
እያሱ ታምሩ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
82′
ተቀይሮ የገባው ትዛዙ መንግስቱ ወጥቶ አብዱልሃኪም ሱልጣን ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
79′
አብዱልከሪም መሀመድ ኳስ ካለ አግባብ አባክነሃል በሚል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

74′ አወት ከመስመር ያሻገረውን ኳስ ፍፁም በጭንቅላቱ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

66′ አማኑኤል ዮሃንስ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ አሰግድ አውጥቶበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
58′
አሰግድ አክሊሉ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!! ቡና
58′ ጋቶች ፓኖም የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ፍፁም ቅጣት ምት
56′
ሳዲቅ ላይ በተሰራ ጥፋት ለቡና የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡

52′ ማንኮ ያሻገረለትን ኳስ ፍፁም አየር ላይ እንዳለ መትቶ ሄሱ አውጥቶበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
51′
ሀብታሙ መንገሻ ወጥቶ ትዛዙ መንግስቱ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

— – – – – – –
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቡና
43′
ያቡን ዊልያም ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ ገብቷል፡፡

35′ ያቡን ዊልያም ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ አሰግድ በግሩም ሁኔታ አድኖታል፡፡

22′ የጨዋታው እንቅስቃሴ በመሃል ሜዳ የተገደበ እና የግብ እድሎች የማይፈጠሩበት ሆኗል፡፡

15′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡

6′ ፍፁም ገብረማርያም ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው ሞቅ ባለ የደጋፊ ድባብ ተጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ

ሀሪሰን ሄሱ

አህመድ ረሺድ – ኢኮ ፊቨር – ኤፍሬም ወንድወሰን – አብዱልከሪም መሀመድ

ጋቶች ፓኖም – ኤልያስ ማሞ – መስኡድ መሀመድ

አማኑኤል ዮሃንስ – ያቤውን ዊልያም – እያሱ ታምሩ

የኤሌክትሪክ አሰላለፍ

አሰግድ አክሊሉ

አወት ገ/ሚካኤል – በረከት ተሰማ – ሲሴይ ሀሰን – ተስፋዬ መላኩ

ማንክ ክዌሳ – አዲስ ነጋሽ – ብሩክ አየለ

ሀብታሙ መንገሻ – ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ

One thought on “ኢትዮጵያ ቡና ከ ኤሌክትሪክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

Leave a Reply

error: