ዳዊት ፍቃዱ እና ወልዋሎ ተለያዩ

በክረምቱ ሀዋሳ ከተማን በመልቀቅ ወደ ወልዋሎ አምርቶ የነበረው ዳዊት ፍቃዱ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ የቅርብ ዓመታት ስኬታማ አጥቂዎች መካከል የሚመደበው የቀድሞው የአየር ኃይል እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ዳዊት ፍቃዱ ከ7 መልካም የውድድር ዓመታት በኋላ ደደቢትን በመልቀቅ አምና ወደ ሀዋሳ ከተማ በማምራት የተጫወተ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ወልዋሎን በአንድ ዓመት የውል ኮንትራት ተቀላቅሎ ነበር፡፡ በክለቡ ጥቂት ጨዋታዎችን ያደረገው ተጫዋቹ በሜዳ ላይ የተጠበቀው መሆን እንዳይችል ጉዳት በተደጋጋሚ እያጠቃው በመሆኑና ተጫዋቹም በክለቡ ደስተኛ ባለመሆኑ ምክንያት ከክለቡ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በስምምነት ለመለያየት በመወሰናቸው ሊለያዩ መቻላቸውን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ ተጫዋቹ በቀጣይ ወደየትኛው ክለብ ሊያመራ ይችላል ቢባልም ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት እረፍት ማድረግ ምርጫው ምሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *