ጅማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግን በበላይነት አጠናቆ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው ጅማ ከተማ በተጫዋቾች ዝውውር ላይ መሳተፍ ጀምሯል፡፡ ቢንያም ሲራጅ እና አሸናፊ ሽብሩ ደግሞ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወላይታ ድቻን ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በማምራት ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በቀይ እና ነጭ ለባሾቹ ቤት ያሳለፈው የተከላካይ አማካዩ አሸናፊ ኮንትራቱን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለአዲስ አዳጊው ክለብ መፈረሙ ተረጋግጧል፡፡

ቢንያም ሲራጅ በሐረር ቢራ (ሐረር ሲቲ) እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለረጅም አመታት የመጫወት ልምድ ያለው የመሀል ተከላካይ ሲሆን ከፕሪምየር ሊጉ የወረደው ንግድ ባንክን ለቆ ለጅማ ከተማ ፊርማውን አኑሯል፡፡

ጅማ ከተማ በቀጣዩ የውድድር አመት በሊጉ ለመደላደል በማሰብ በርካታ የሊጉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ሲገኝ የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር በቀጣይ ቀናት ይፋ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *