ለገጣፎ ለገዳዲ ሁለት ተጫዋቾች ሲያስፈርም የበርካታ ነባሮችን ውል አድሷል

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ተወዳዳሪ ለገጣፎ ለገዳዲ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም 13 ነባሮች ውላቸውን አድሰዋል።

ሳዲቅ ተማም ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል። የአጥቂ መስመር ተሰላፊው በለገጣፎ ጥሩ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ወደ ባህር ዳር ከተማ አምርቶ ብዙም ሳይቆይ ወደ ለገጣፎ የተመለሰ ሲሆን ዓምና በኤሌክትሪክ አሳልፎ ለሦስተኛ ጊዜ ለገጣፎን ተቀላቅሏል።

ሌላኛው ፈራሚ ሀብታሙ ወርቁ ነው። የአጥዚ መስመር ተሰላፊው ያለፉትን ዓመታት በወሎ ኮምቦልቻ በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ጎል አስቆጣሪያቸው ልደቱ ለማን ወደ መከላከያ ለሸኙት ለገጣፎዎች ጥሩ አማራጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ውላቸውን ያራዘሙ:- ተመስገን አዳሙ፣ ወንደሰወሰን ቦጋለ፣ ሚኪያስ ፍቅሬ፣ መዝገቡ ቶላ፣ ጌትነት ደጀኔ፣ ታምሩ ቅባቱ፣ ወንድማገኝ ግርማ (ተከላካዮች)፣ ፍቅሩ ዓለማየሁ፣ ሽመክት ግርማ፣ ዘካርያስ ከበደ፣ በሱፍቃድ ነጋሽ (አማካዮች)፣ ዳዊት ቀለመወርቅ እና ፋሲል አስማማው (አጥቂዎች)

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!