ቴዎድሮስ በቀለ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል

በዝውውር መስኮቱ ሙጂብ ቃሲምን ወደ ፋሲል የሸኘው አዳማ ከተማ ቀጥተኛ ተተኪ ያገኘ ይመስላል። 
ሲሳይ አብርሀምን አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረው አዳማ ከተማ ቴዎድሮስ በቀለን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል። የግራ እግር ተጫዋቹ በመከላከያ ወሳኝ ተጫዋች ሆኖ ቢቆይም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጉዳት እምብዛም ግልጋሎት መስጠት አልቻለም። በጦሩ ቤት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎም ወደ አዳማ አምርቷል።

ቴዎድሮስ በመሐል ተከላካይ እና የግራ መስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ በሚጫወት በመሆኑ ተመሳሳይ ሚናዎችን መወጣት የሚችለው ሙጂብ ቃሲምን እንደሚተካ ታምኖበታል።

እስካሁን ሁለት ተጫዋቾች ያስፈረመው አዳማ የመሐል ተከላካዩ ምኞት ደበበን ውልም አራዝሟል።