ምንይሉ ወንድሙ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አድርጓል

የመከላከያው አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አበርክቷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ለማጥፋት የእግር ኳስ ቤተሰቡ ድጋፍ እያደረገ ሲሆን የመከላከያው አጥቂ ምንይሉ ወንድሙም ድጋፍ አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ ባለፈው ሳምንት ለትውልድ ስፍራው ጅማ ከተማ የገንዘብ ስጦታን ያበረከተ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በዛው ጅማ አቅመ ደካማ ለሆኑ እና ከቤት መውጣት ለማይችሉ አረጋውያን የንፅህና መጠበቂያዎችን እና ምግብ ነክ ነገሮችን ነው የለገሰው፡፡ ተጫዋቹ ከዚህ በተሻለ በቀጣይም በሽታው እስኪጠፋ ርብርብ እንደሚያደርግም ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ