ሰበታ ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ከአዳማ ከተማ ታዳጊ ቡድን የተገኙት ፉአድ ፈረጃ እና ቡልቻ ሹራ የሰበታ ከተማ አዳዲስ ፈራሚ ለመሆን ተስማምተዋል፡፡

ከአዳማ ከተማ ታዳጊ ቡድን በ2010 ካደገ በኃላ ፈጣን ዕድገት በማሳየት በዋናው ቡድን መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው ወጣቱ አማካይ ፉአድ ፈረጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በቅርቡ ተጠርቶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ተጫዋቹ ውሉ በአዳማ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው ወደ ሰበታ ከተማ ለማምራት የተስማማው፡፡

የመስመር እና የፊት አጥቂው ቡልቻ ሹራ ወደ ሰበታ ለማምራት የተስማማ ሦስተኛ ፈራሚ ሆኗል፡፡ በ2008 በአዳማ ወጣት ቡድን ባሳየው ድንቅ አቋም ካደገ በኃላ በሊጉ ድንቅ ዓመታትን ያሳለፈው ተጫዋቹ ውሉ በመጠናቀቁ ወደ ሰበታ ከተማ ተጉዟል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ