መልካሙ ታውፈር በጣሊያን ለታችኛው ዲቪዚዮን ክለብ ፈርሟል

ዓምና ለፋሲል ከነማ ፈርሞ ምንም ጨዋታ ሳያደርግ ከዐፄዎቹ ጋር የተለያየው መልካሙ በጣልያን አዲስ ክለብ አግኝቷል።

ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ከዓመታት በፊት የተለያቸው ቤተሰቦቹን ያገኘው መልካሙ ታውፈር በፋሲል ከነማ ቤት የሙከራ አድል አግኝቶ ሙከራውን ካጠናቀቀ በኋላ ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ፊርማ መፈረሙ የሚታወስ ነው። በፋሲል የጠበቀውን የመሰለፍ አድል ያላገኘው መልካሙ ወደ ክለቡ እንደመጣ ጉዳት አጋጥሞት ወደ ጣሊያን በመመለሱ ምክንያት የቅድመ ወድድር ዝግጅት ላይ አለመገኘቱንና እና በጉዳትም ለጨዋታ ብቁ ባለመሆኑ የመጫወት እድል ሳያገኝ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ፋሲል ከነማ ገልጾልናል።

መልካሙ ወደ ጣልያን ተመልሶ የፈረመበት አዲስ ክለብ በአራተኛ ዲቪዚዮን የሚጫወተው ሲሊቨርጌ ካልቺዮ የሚባል ሲሆን ክለቡም በዌብሳይቱ መልካሙን በማስፈረማቸው ደስተኛ መሆናቸውንና ከቀድሞ ክለቡ አርዛኬና እና ፋሲል ከነማ እንዲሁም ባደገበት ኢንተር ሚላን ያገኘውን ልምድ በመጠቀም ክለብን እንደሚጠቅም እምነታቸውን ገልፀዋል ።

መልካሙ ከዚህ ቀደም ለኢንተር ሚላን ታዳጊ ቡድን፣ ለጣሊያን ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን፣ አርዛኬና እና ፋሲል ከነማ ተጫውቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!