የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ነገ ይጀመራል፡፡
ከሁለት ዞኖች በተውጣጡ 10 ክለቦች መካከል የሚካሄደው የማጠቀለያ ውድድሩ ከሰኔ 11-26 የሚካሄድ ሲሆን የምድብ ድልድሉ በውድድሩ ደንብ መሰረት ወጥቷል፡፡
የምድብ ድልድል
ምድብ ሀ
ደደቢት ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ መከላከያ
ምድብ ለ
ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ ፣ ዳሽን ቢራ
የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ዛሬ 11:00 ላይ በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገላጋይ ፣ የሊግ ኮሚቴ አባላት ፣ የዳኞች ማህበር ፣ የክልሉ ፀጥታ አካላት ፣ የቡድን መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በዚህም መሰረት በመክፈቻ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከዳሽን ቢራ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ይፋለማሉ፡፡
ለ15 ቀናት በሚቆየው ውድድር በየምድብ ጨዋታዎች 1 ቡድን የሚያርፍ ሲሆን ከመክፈቻው በኀላ የሚደረጉ ጨዋታዎች ወደ ሀዋሳ ከተማ ስታድየም (ሰው ሰራሽ ሜዳ) ይዞራሉ፡፡
የነገ ጨዋታዎች
08:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
10:00 ኤሌትሪክ ከ ዳሽን ቢራ