ጋቶች ፓኖም ወደ ፈረሰኞቹ ያመራል

ጋቶች ፓኖም ወደ ፈረሰኞቹ ያመራል

የግዙፉ ተከላካይ አማካይ አዲስ ክለብ ታውቋል

 

ባሳለፍነው ዓመት ከኢትዮጵያ መድን ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ወደ ኢራቅ በማቅናት በስታርስ ሊግ ተሳታፊ በሆኑት ኒው ሮዝ እና አል ናጃፍ ጥሩ ቆይታ ያደረገው ጋቶች ፓኖም የሳውዲ አረብያው ክለብ ለመቀላቀል ወደ ስፍራው ማቅናቱን ዘግበንላቹሁ ነበር። ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ መሰረት የጋቶች ፓኖው ማረፍያ አል አረቢያ ስፖርት ክለብ መሆኑ አረጋግጣለች።

አል አረቢያ በሳውዲ አረቢያ አል ቃሲም ግዛት ውስጥ በምትገኘው ውቢቷ ኡናይዛህ ከተማ የሚገኝ የ68 ዓመታት ዕድሜ ያለው አንጋፋ ክለብ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በሳውዲ አረቢያ የመጀመሪያ ዲቪዚዮን (ሁለተኛው ዕርከን) ላይ በመወዳደር ይገኛል።

በአሰልጣኝ ጋዚ ግራይሪ ወደ ሚመሩት የኡናይዛህ ፈረሰኞች ያቀናው ኢትዮጵያዊ አማካይ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ቡና፣ በሩሲያው አንዚ ማካቻካላ፣ በግብፅ ክለቦች ኤልጎውና እና ሀራስ ኤል ሁዳድ በሳውዲው አል አንዋር እንዲሁም በሀገራችን ክለቦች መቐለ 70 እንደርታ ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ መድን መጫወቱ ይታወቃል።