የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ነገ ይጀመራል

የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ነገ ይጀመራል፡፡

ከሁለት ዞኖች በተውጣጡ 10 ክለቦች መካከል የሚካሄደው የማጠቀለያ ውድድሩ ከሰኔ 11-26 የሚካሄድ ሲሆን የምድብ ድልድሉ በውድድሩ ደንብ መሰረት ወጥቷል፡፡


የምድብ ድልድል

ምድብ ሀ

ደደቢት ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ መከላከያ

ምድብ ለ

ሀዋሳ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ ፣ ዳሽን ቢራ


የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ዛሬ 11:00 ላይ በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገላጋይ ፣ የሊግ ኮሚቴ አባላት ፣ የዳኞች ማህበር ፣  የክልሉ ፀጥታ አካላት ፣ የቡድን መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በዚህም መሰረት በመክፈቻ ጨዋታዎች ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከዳሽን ቢራ በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም ይፋለማሉ፡፡

ለ15 ቀናት በሚቆየው ውድድር በየምድብ ጨዋታዎች 1 ቡድን የሚያርፍ ሲሆን ከመክፈቻው በኀላ የሚደረጉ ጨዋታዎች ወደ ሀዋሳ ከተማ ስታድየም (ሰው ሰራሽ ሜዳ) ይዞራሉ፡፡

 

የነገ ጨዋታዎች

08:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

10:00 ኤሌትሪክ ከ ዳሽን ቢራ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *