የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ጥሎ ማለፍ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ውድድር የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ ከጥሎ ማለፉ እጣ ማውጣትም ባለፈ የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር የሚጀመርበት ጊዜ ይፋ ሆኗል፡፡

በሁለት ምድብ ተከፍለው ውድድራቸውን ሲያደርጉ የነበሩ 15 ክለቦች በጥሎ ማለፉ ላይ ይሳተፋሉ፡፡ ወደ ክልል ተጎዞ መጫወት እና ሁሉም ጨዋታዎች አዲስ አበባ ላይ ይካሄዱ በሚለው ጉዳይ ላይ ክለቦች ሃሳባቸውን የሰጡ ሲሆን ውድድሩ በአዲስ አበባ እና በክልል ክለብ ሜዳዎች የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡

የእጣው ስነ-ስርዓት የተደረገው ክለቦቹ በመጀመሪያው ዙር በሊጉ ላይ ባስመዘገቡት ውጤት ነው፡፡ በዕጣው መሰረት ኒያላ በቀጥታ ወደ ሩብ ፍፃሜ ሲያልፍ ሁለት ጨዋታዎች ብቻ በክልል ከተሞች የሚካሄዱ ይሆናል፡፡

በተያያዘ የፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዙር መጋቢት 3 ይጀምራል፡፡ ምድብ ሀን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ16 ነጥብ ሲመራ ወላይታ ድቻ በእኩል 16 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ነው፡፡ መከላከያ በ15 ነጥብ ሶስተኛ ነው፡፡ ምድብ ለን አዳማ ከተማ ተከታዮን ቅዱስ ጊዮርጊስን በሁለት ነጥብ በመብለጥ በ14 ነጥብ መሪ ሲሆን ኒያላ በ9 ነጥብ ሶሰተኛ ነው፡፡

ተመስገን ዘውዱ ከባንክ በ10 ግቦች የምድብ ሀን ኮከብ ግብ አግቢነት ሲመራ ቅዱስ ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ቡና እና አቤል ነጋሽ ከመከላከያ በ7 ግቦች ይከተላሉ፡፡ በረከት ማህተሜ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና አቤኔዘር ሲሳይ ከአዳማ ከተማ በ5 ግቦች የምድብ ለን ደረጃ በቀዳሚነት ይዘዋል፡፡ አብዱልመጅድ ሁሴን (ኒያላ)፣ አሸናፊ ጉታ (አዲስ አበባ ከተማ)፣ አደም አመስ (የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ) እና አብዱልከሪም አብደላ (አዳማ ከተማ) በእኩል ሶስት ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡

የጥሎ ማለፉ ድልድል ይህንን ይመስላል (አወዳዳሪው አካል የቀን እና የቦታ ለውጥ ሊያደረግ ይችላል)

የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ (13/9/09)

ኢትዮጵያ መድን ከ አዲስ አበባ ከተማ (አዲስ አበባ)

ደደቢት ከ አዳማ ከተማ (አዲስ አበባ)

ሀረር ሲቲ ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ (አዲስ አበባ)

ኢትዮጵያ ቡና ከ መከላከያ (አዲስ አበባ)

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አፍሮ ፂዮን ኮንስትራክሽን (አዲስ አበባ)

ሀዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ሀዋሳ)

ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ (ሶዶ)

ሩብ ፍፃሜ (በ20/9/09)

(1) ኒያላ ከ ኢትዮጵያ መድን እና አዲስ አበባ ከተማ አሸናፊ

(2) የደደቢት እና አዳማ ከተማ አሸናፊ ከ ሀረር ሲቲ እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አሸናፊ

(3) የኢትዮጵያ ቡና እና መከላከያ አሸናፊ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አፍሮ ፂዮን ኮንስትራክሽን አሸናፊ

(4) የሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ ከ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አሸናፊ

ግማሽ ፍፃሜ (በ27/09/09)

(5) የጨዋታ 1 አሸናፊ ከ ጨዋታ 2 አሸናፊ

(6) የጨዋታ 3 አሸናፊ ከ ጨዋታ 4 አሸናፊ

ፍፃሜ

የጨዋታ 5 አሸናፊ ከ ጨዋታ 6 አሸናፊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *