በሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ ቦሌ እና ቅድስት ማርያም አሸንፈዋል

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሲገባደድ ቦሌ ክፍለ ከተማ እና ቅድስት ማርያም ድል አድርገዋል፡፡

05:00 ላይ በአአ ስታድየም ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመው ቦሌ ክፍለከተማ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡ ቤተልሄም መንተሎ በ22ኛው እና 33ኛው ደቂቃ ባስቆጠረቻቸው ግቦች ለእረፍት 2-0 ሲወጡ ምንትዋብ  ዮሃንስ በ59ኛው እንዲሁም መድሀኒት አውታሬ በ90ኛው ደቂቃ ተጨማሪ ግቦች አክለው ጨዋታው በቦሌ ክፍለከተማ 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

08:30 ላይ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ከ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ያደረጉት ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር አስተናግዶ በቅድስት ማርያም 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቅድስት ማርያም በመዲና አወል እና እድላዊት ለማ ባስቆጠሯቸው ግቦች እስከ 73ኛው ደቂቃ 2-0 መምራት ቢችሉም ወርቅነሽ መሰለ እና አበራሽ አበበ አከታትለው ያስቆጠሯቸው ግቦች አቃቂ ቃሊቲን ወደ ጨዋታው መመለስ ችለው ነበር፡፡ ሆኖም አምበሏ ማህሌት ታደሰ ባስቆጠረችው ቅጣት ምት ቅድስት ማርያም 3-2 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፍ ረድታለች፡፡ በጨዋታው የቅድስት ማርያሙ አሰልጣኝ ዮናስ ወርቁ የዘርሃረግ ተካልኝን ቀይሮ ባስገባ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ መልሶ ቀይሮ ማስወጣቱ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡

[table “243” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ለ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
136276383186587
236207969264367
336158134449-553
436147154453-949
536129153646-1045
6189272521429
71861111933-1419
81851123249-1716
91822141544-298
101821151354-417

በእለቱ የመጨረሻ መርሃ ግብር 10:30 ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረች ግብ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ነጥብ ተጋቷል፡፡

እምብዛም ሳቢ ያልነበረው የሁለቱ ቡድኖች የመጀመርያው አጋማሽ ጨዋታ ግብ ያልተቆጠረበት ሲሆን የተሻለ ፉክክር በተስተናገደበት ሁለተኛው አጋማሽ በጨዋታው በግሏ ጥረት ስታደርግ የነበረችው ታታሪዋ አጥቂ ሲሳይ ገብረዋሀድ በ74ኛው ደቂቃ አካዳሚን ቀዳሚ ያደረገች ሲሆን ጨዋታውም በዚሁ ውጤት የሚጠናቀቅ መስሎ ነበር፡፡ ሆኖም ተቀይራ የገባችው ስንታየሁ ኢራኮ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 1 ደቂቃ ሲቀረው ባስቆጠረችው ግብ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡

[table “233” not found /]

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ – ምድብ ሀ

#ክለብተጫአሸአቻተሸአስተቆልዩነጥብ
13630601141410096
2361791054381660
3361851361441759
436156154356-1351
5361211135052-247
6187472724325
71852111632-1617
81843112245-2315
91813141141-306
10180513847-395

Leave a Reply