​የሴቶች ዝውውር | ኤሌክትሪክ የ16 ተጫዋቾቸን ውል ሲያድስ አንድ ተጫዋች አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የተጠናቀቀው የውድድር አመት ከፍተኛ መሻሻል ካሳየዩ ቡድኖች መካከል የሚጠቀሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአስራ ስድስት ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ አንድ አዲስ ተጫዋች ማስፈረሙ ታውቋል፡፡

በቡድኑ ውስጥ ግልጋሎት ይሰጡ የነበሩና በውድድር አመቱ መገባደጃ ውላቸው የተጠናቀቁ 16 ተጫዋቾች ለቀጣይ ሁለት አመታት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት ፊርማቸው አኑረዋል፡፡
ከነዚህ ተጫዋቾች በተጨማሪ ቡድኑን ለማጠናከር በደደቢት የሴቶች ቡድን ውስጥ በአመዛኙ የመሰለፍ እድልን ሳታገኝ ከተቀያሪ ወንበር እየተነሳች ስታገለግል የነበረችውን ታታሪዋ ትበይን መስፍን ማስፈረማቸው ታውቋል፡፡ ክለቡ ከዚህ በኃላ የክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት እስኪዘጋ ባሉት ጊዜያት ተጨማሪ ተጫዋቾችን እንደማያስፈርምም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ክለቡ የተጫዋቾቹን የደሞዝ ስኬል ዳግም በመከለስ የቡድኑ ቋሚ ተጫዋቾች ለሆኑ ተጫዋቾች 15,000 ብር፣ ከተቀያሪ ወንበር እየተነሱ ለሚጫወቱ ተጫዋቾች 9,000 ብር እንዲሁም ለቀሩት የቡድኑ ተጫዋቾች 7,500 ወርሃዊ ደሞዝ እንደሚከፍል አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *