ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው ተጫዋች ወደ አዳማ ከተማ ለማምራት ተስማምቷል።
አሰልጣኝ ስዩም ከበደን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥረው እስካሁን ድረስ በዝውውር መስኮቱ ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት አዳማ ከተማዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው አማካዩ ፍቅረየሱስ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ30 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2253′ ደቂቃዎችን ቡድኑን በማገልገል በፕሪምየር ሊጉ 4 ግቦች በማስቆጠር ቡድኑ በኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ ፍፃሜው እንዲጓዝ ጉልህ አስተዋጾ ያበረከተው አማካዩ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ጥሩ እንቅስቃሴ ካደረገ በኋላ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለውን ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ማረፍያው አዳማ ከተማ ሆኗል። ተጫዋቹ ከዚህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሲድማ ቡና ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።