ሽረ ምድረ ገነት የነባር ተጫዋቾች ውል አድሷል

ሽረ ምድረ ገነት የነባር ተጫዋቾች ውል አድሷል

ሽረ ምድረ ገነቶች አንድ ተጫዋች አስፈርመው የስድስት ነባር ተጫዋቾች ውል አራዝመዋል።

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በርከት ያሉ ተጫዋቾች ያስፈረሙት በአሰልጣኝ ዳንኤል ፀሐዬ የሚመሩት ስሑል ሽረዎች አሁን ደግሞ ፊታቸውን የነባር ተጫዋቾች ውል ወደ ማራዘም አዙረው የስድስት ተጫዋቾች ውል አራዝመው አንድ ተጫዋች አስፈርመዋል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ያሳለፈው የመስመር ተጫዋቹ ናትናኤል ተኽለ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ሽረ ምድረገነት ተመልሷል። ውላቸውን ለማራዘም የተስማሙት ተጫዋቾች ደግሞ ባለፉት ዓመታት ቡድኑን ያገለገሉት አጥቂው ብሩክ ሐድሽ፣ ግብ ጠባቂው ዋልታ ዓንደይ፣ በመስመር ተከላካይነት እና መስመር ተጫዋች ሆኖ መጫወት የሚችለው ሁለገቡ ክፍሎም ገብረህይወት፣ የመሀል ተከላካዩ ክብሮም ብርሀነ እንዲሁም አማካዮቹ ኬቨን አርጉዲ እና ጎይትኦም ነጋ ከቡድኑ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት የተስማሙ ተጫዋቾች ናቸው።