ቤተ ኢስራኤላዊው የኢሬዲቪዚውን ክለብ ተቀላቀለ

ቤተ ኢስራኤላዊው የኢሬዲቪዚውን ክለብ ተቀላቀለ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወደ ኔዘርላንድ አምርቷል።

በርከት ያሉ ተከላካዮቹን በጉዳት ያጣው የኔዘርላንዱ ክለብ  ኔይመኸ ትውልደ ኢትዮጵያዊው የቀኝ መስመር ተከላካይ አላዛር ዳሳ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል። ከሩስያው ክለብ ዳይናሞ ሞስኮ ጋር የነበረው ውል ከተጠናቀቀ በኋላ ከውል ነፃ ሆኖ የቆየው ይህ የ32 ዓመት ተከላካይ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የማራዘም አማራጭ ባካተተ የአንድ ዓመት ውል የኔዘርላንዱን ክለብ ተቀላቅሏል።

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰብ የተወለደውና በቤይታር ጄሩሳሌም እግር ኳስ ጀምሮ ቀጥሎም በማካቢ ቴል አቪቭ፣ ቪትሰ፣ ዳይናሞ ሞስኮ እንዲሁም በኢስራኤል ብሔራዊ ቡድን መጫወት የቻለው ይህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በአውሮፓ ቻምፕዮንስ ሊግ፣ ኮንፈረንስ ሊግ እና የአውሮፓ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ የመሳተፍ ልምድ ያለው ተጫዋች ነው።

ለእስራኤል ብሔራዊ ቡድን 71 ጨዋታዎች ማከናወን የቻለው እና በአሁኑ ወቅት ብሔራዊ ቡድኑን በአምበልነት በመምራት ላይ የሚገኘው አላዛር እስራኤልን በአምበልነት የመራ በታሪክ የመጀመርያው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሲሆን
አሁን ደግሞ በቪትሰ ቆይታው የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ከሰሩት የወቅቱ የኔይመኸን ዋና አሰልጣኝ ዲክ ሽሬይደር ጋር ዳግም ለመስራት በነፃ ዝውውር ቡድኑን ተቀላቅሏል።