ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንድ ተጫዋች ከዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ውጭ ሆነ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ዛሬ ዝግጅቱን መጀመሩ ይታወቃል፤ ቡድኑ ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መድኑን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራን በጉዳት ማጣቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ያሬድ ካሳዬን በጉዳት ምክንያት ከማጣርያ ውድድር ውጭ ሆኗል።
ኢትዮጵያ መድን ከዛምዚባሩ ምላንዴግ ጋር ባደረገው የካፍ ቶታል ቻምፕዮንስ ሊግ የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታ ላይ ጉዳት ያስተናገደው ተጫዋቹ ጉዳቱ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል ባይታወቅም ከዓለም ዋንጫው የመጨረሻ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ውጭ መሆኑ ታውቋል።