የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ ነገ የልምምድ ጨዋታ ያደርጋል።
በቀጣይ ከጊኒ ቢሳው እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርጋቸው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ዝግጅታቸውን የጀመሩት ዋልያዎቹ ነገ የልምምድ ጨዋታ እንደሚያደርጉ አውቀናል።
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውንም በአዲስ አበባ ከተማ የሕዳሴ ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ከሚገኘው እና ነገ አራፊ ከሆነው ኢትዮጵያ ቡና ጋር ነገ ረፋድ 3:30 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ቢሳው ጋር በሩዋንዳው አማሆሮ ስታዲየም መስከረም 28 ቀን ለሚያከናውነው ጨዋታ ሰኞ ወደ ስፍራው እንደሚያቀና ይጠበቃል።