አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወሳኝ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ይመራሉ።
አራት ኢትዮጵያውያን ዳኞች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ይመራሉ። መስከረም 28 ሞሪሽየስ ከ ካሜሩን የሚያካሂዱት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ አራት ኢንተርናሽናል ዳኞች ይመሩታል። በቅርቡ የአልጀርያው ቤሎዚዳድ ከ ቡርኪናፋሶው ዶዋንስ በሚሎድ ሀደፊ ስቴድየም ያካሂዱት የካፍ ቶታል ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በጣምራ የመሩት ኢንተርናሽናል ዳኞች ቴዎድሮስ ምትኩ በዋና ዳኝነት፤ ፋሲካ የኋላሸት ደግሞ በረዳት ዳኝነት እንዲሁም ኢንተርናሽናል ዳኞች አሸብር ታፈሰ በረዳትነት ፤ በላይ ታደሰ ደግሞ በአራተኛ ዳኛነት ጨዋታውን የሚመሩት ሲሆን ጨዋታውም መስከረም 28 በኮት ዲ ኦር ብሔራዊ የስፖርት ኮምፕሌክስ ውስጥ በሚገኘው ‘National Sports Complex Pitch 1’ ይካሄዳል።