አዲስ ተጫዋች ወደ ዋልያዎቹ ስብስብ ተቀላቅሏል

አዲስ ተጫዋች ወደ ዋልያዎቹ ስብስብ ተቀላቅሏል

የሦስተኛ ቀን ልምምዱን እየሰራ በሚገኘው ብሔራዊ ቡድናችን ዙሪያ አዲስ መረጃ እናድርሳቹሁ

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሐሌ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ላለበት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ ውድድር ሰኞ ዝግጅት መጀመሩ ይታወቃል። ዋልያዎቹ ዝግጅት ከጀመሩ ዛሬ ሦስተኛ ቀን ያስቆጠሩ ሲሆን ጠዋት በአዲስ አበባ ስታዲየም ልምምዳቸውን ሲሰሩ አርፍደው አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የቀኑ ሁለተኛ ልምምዳቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

 

ቀደም ብለን ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል የሆኑት ጋቶች ፓኖም እና ከነአን ማርክነህ ከሰሞኑ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ መግለፃችን የሚታወስ ሲሆን አሁን ባገኘነው መረጃ መሰረት ደግሞ በሳውዲ አረቢያ ሁለተኛ ሊግ በአል አረቢያ ስፖርት ክለብ የሚገኘው ጋቶች ፓኖም ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል። ተጫዋቹ ከጉዞ ድካም ጋር በተያያዘ ዛሬ ዕረፍት አድርጎ ነገ ልምምድ ይጀምራል ተብሎ ቢጠበቅም በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል የመጀመርያው ልምምዱን እየሰራ ይገኛል።