በተጠናቀቀው ዓመት ከሲዳማ ቡና ጋር ቆይታ የነበረው ካሜሮናዊውን አጥቂ ውሉን ለማራዘም እንደተስማማ ታውቋል
ለሀገሩ ክለቦች ዩኒየን ዶውላ እና ዳይናሞ ዶውላ የተጫወተው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሲዳማ ቡናን በመቀላቀል ከቡድኑ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ካሜሮናዊ አጥቂ ብለስ ናጎ ከቡድኑ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል።። ተጫዋቹ በተጠናቀቀው ዓመት በሠላሳ ሦስት ጨዋታዎች ተሳትፎ 2139 ደቂቃዎች ሜዳ ላይ መቆየቱ ይታወሳል።
ሲዳማ ቡናዎች በአፍሪካ መድረክ እና በሀገር ውስጥ ለሚጠብቋቸው ውድድሮች ወደ ዝውውሩ አስቀድመው በመግባት የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን መስፍን ታፈሰን ፣ ያሬድ ባዬ፣ ደስታ ደሙ፣ አስቻለው ሙሴ እና መላኩ አሰፋ ውል ሲያራዝሙ ኤፍሬም ታምራት እና ውብሸት ክፍሌ ለማስፈረም መስማማታቸው ሲታወቅ የኋላ ኋላ ግን በክረምቱ በዝውውሩ ተቀዛቅዘው ይገኛሉ።

