የ2019 የውድድር ዘመን መርሐ ግብር ሲዘጋጅ ምን ምን ጉዳዮች ታሳቢ ተደርገው ነው?

የ2019 የውድድር ዘመን መርሐ ግብር ሲዘጋጅ ምን ምን ጉዳዮች ታሳቢ ተደርገው ነው?

ለየት ባለ ቅርፅ እና አካሄድ የሚደረገው የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሲዘጋጅ መነሻ ሀሳቦቹ ምንድን ናቸው?

በ7 ስታዲየሞች እና በ18 ክለቦች መካከል የሚደረገው የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ከደቂቃዎች በፊት የወጣ ሲሆን መርሐ ግብሩ ሲወጣ ታሳቢ የተደረጉ ነገሮችን ሊጉ ገለፃ አድርጓል።

በዚህም በዋናነት ​የሊጉ ክለቦች በሚገኙባቸው ከተሞች መካከል ያለውን የጉዞ ርቀትን፣ ​ክለቦች የሚያደርጉትን ጨዋታ በመረጡት ስታዲየም በአብዛኛው በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የሚጫወቱበትን አማራጭ፣​ የብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ዋንጫ ጨዋታዎች፣ ​በኢንተርናሽናል ውድድር በሚሳተፉ ክለቦች ምክንያት ሊኖር የሚችለውን ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ​ውድድሩን ከግንቦት 30 በፊት ለማጠናቀቅ የሚቻልበትን አማራጭ እና ​መነሻ ሀሳቦች መሠረት አድርጎ መርሐ ግብሩ እንደወጣ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መርሐ ግብሮቹ በአብዛኛው ዓርብ፣ ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ እንዲውሉ መደረጉንና የጨዋታ ሰዓቶቹም ለተመልካች ምቹ የሆኑ ሰዓቶች እንደተመረጡ ተመላክቷል (መብራት ያላቸው ሜዳዎች ላይ ደግሞ ማታ)።

የሊጉ ውድድር መስከረም 30 እንደሚጀምር ቢገለፅም ዛሬ ውድድሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መስከረም 29 እንደሚጀምርም ታውቋል።