በአሰልጣኝ ፋሲን ተካልኝ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ሴኔጋላዊ ግብ ጠባቂ አስፈረሙ

የቀድሞ አሰልጣኛቸው ፋሲል ተካልኝ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በመሾም ለ2019 የውድድር ዓመት ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች ሴኔጋላዊ ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል። ወደ ቡድኑ የተቀላቀለው በሀገሩ ክለቦች ሶናኮስ፣ ሳሎም እና ጃራፍ የተጫወተው አብዱላይ ዲያካቴ ነው። በጃራፍ ቆይታው የሴኔጋል ሊግ 1 እና የሴኔጋል ዋንጫ ያሸነፈው ይህ ግብ ጠባቂ አሁን ደግሞ አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ከስምምነት ተደርሷል።

