አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ምን አሉ?

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ምን አሉ?

“የግብ ጠባቂዎች ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው ፤ ከ18 ክለብ 16ቱ የውጪ ሀገር ግብጠባቂ ነው ሚጠቀሙት።”

“በትውልደ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ብዙ ጥያቄዎች እየደረሱኝ ነው ሆኖም ሕጉ ካልተስተካከለ እኔ መምረጥ አልችልም።”

በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከሱዳን እና ከሴኔጋል ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ዮሐንስ ሳሕሌ በጉባዔው ይህንን ብለዋል።

“ብሔራዊ ቡድናችን የክለቦች ስብስብ ነው። ክለቦች ናቸው ብሔራዊ ቡድኑን አንድ የሚያደርጉት። ክለቦችን ማሳስበው ግብ ጠባቂዎችን የሚያፈሩበት መንገድ ይታሰብበት ከ18ቱ ክለቦች 16ቱ የውጪ ሀገር ግብ ጠባቂዎች ናቸው። ትውልደ ኢትዮጵውያንን በተመለከተ እኛ መምረጥ አንችልም በእግርኳስ ፌዴሬሽኑ እና በመንግሥት መካከል ድርድር አለ ፤ እሱ አልገባኝም መላው ዓለም የሚጠቀምበትን ባለመጠቀማችን። 40 የሚሆኑ በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚጫወቱ እንዲሁም 50 የሚሆኑ ከ17-19 ዕድሜ ያሉ ታዳጊዎች ለሀገራችን ለመጫወት ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን ዴቪድ በሻህ አሳውቆኛል።”