ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወሳኙን ጨዋታ ይመራሉ

ኢትዮጵያውያን ዳኞች ወሳኙን ጨዋታ ይመራሉ

አራት የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ዳኞች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን ይመራሉ

በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች ከሳምንት በኋላ ይጀምራሉ።

በምድብ 12 ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የሚጠበቀው የጊኒ ቢሳውና የናይጄሪያ ጨዋታም በኢትዮጵያውያን ዳኞች እንደሚመራ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

በ “Estádio Nacional 24 de Setembro, Bissau” የሚካሄደውን ጨዋታ በዋና ዳኝነት ቴዎድሮስ ምትኩ ፣ በረዳት ዳኝነት ትግል ግዛው እና ፋሲካ የኋላሸት እንዲሁም በአራተኛ ዳኝነት ማኑሄ ወልደጻድቅ የሚመሩት ሲሆን ጨዋታው መስከረም 19 ከቀኑ 9፡00 ላይ ይደረጋል።