የቴራንጋ አናብስት ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የቴራንጋ አናብስት ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ ሲያደርግ ሳድዮ ማኔ ከስብስቡ ውጭ ሆኗል

አዲሱ የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪየራ ከሞዛምቢክ እና ኢትዮጵያ ጋር ላለባቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች እንዲሁም በፈረንሳይ ማርሴይ ከተማ ከኮሞሮስ ጋር ለሚያደርጉት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ 29 ተጫዋቾች የያዘው ስብስብ ይፋ አድረገ።

በአሰልጣኝነት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከክለብ እግር ኳስ አሰልጣኝነት ወጥቶ የትውልድ ሀገሩን ብሔራዊ ቡድን ለማሰልጠን የተስማማው ፓትሪክ ቪየራ በሳውዲ አርቢያው ክለብ አል ናስር በመጫወት ላይ የሚገኘው ሳድዮ ማኔን ከስብስቡ ውጭ ሲያደርግ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “የመጨረሻው የአፍሪካ ዋንጫ ምርጥ ተጫዋች የሆነው ሳድዮ ማኔ መጠነኛ ጉዳት ገጥሞታል” ብለዋል።