ተጫዋቹ የዋልያዎቹን ካምፕ ተቀላቅሏል

ተጫዋቹ የዋልያዎቹን ካምፕ ተቀላቅሏል

አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የዋልያዎቹ ዝግጅት የመጨረሻው ተጫዋች ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቅሏል።

በሚቀጥለው ዓመት ለሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ምድብ ድልድሉን ለመቀላቀል ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታውን ለማድረግ ከቀናት በፊት ዝግጅቱን የጀመረው ብሔራዊ ቡድኑ አራተኛ ቀን ልምምዱን በአዲስ አበባ ስታዲየም እየሰራ ይገኛል።

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል በኦማን ሊግ ስኬታማ ቆይታ እያደረገ የሚገኘው ከነዓን የዋልያዎቹን ስብስብ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ በመግባት የቡድኑን ካምፕ ተቀላቅሏል። በአሁኑ ሰዓትም በአዲስ አበባ ስታዲየም ብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ እየሰራ ሲገኝ ከነዓን ከመንገዱ ጉዞ ድካም ጋር ተያይዞ ዕረፍት ማድረግ ስላለበት የጠዋቱ ልምምድ አካል አልሆነም። ሆኖም በቂ ዕረፍት ካደረገ በኋላ ከሰዓት በሚኖረው ሁለተኛ ልምምድ ላይ እንደሚሳተፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከነዓን በኦማን ጂንዳል ሊግ ቆይታው 13 ግቦች እንዲሁም በአህጉራዊው ኤስያ ቻሌንጅ ሊግ በተከናወኑ ሦስት ጨዋታዎች 2 ግቦች እና 1 ግብ የሆነ ኳስ በማመቻቸት ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ መሆኑ ይታወቃል።