አራት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውን “FIFA SERIES” ውድድር ለመምራት ከተመረጡ ዳኞች መካከል ሆነዋል

FIFA Series 2026 የተሰኘ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች ውድድር ዘንድሮ በተሻለ ደረጃ በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በሩዋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል። ይህ ፊፋ በ2024 የጀመረው አዲስ ፕሮጀክት በተለያዩ አህጉራት የሚገኙና የመገናኘት ዕድላቸው አነስተኛ የሆኑ ብሔራዊ ቡድኖች እርስ በርስ እንዲጫወቱ ዕድል የሚፈጥር ውድድር ነው።
በዚህ በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ ዝቅ ብለው የሚገኙ ሀገራት ዓለም አቀፍ ልምድ እንዲቀስሙ ለመርዳት የሚዘጋጀው ውድድርም ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በዚህ ወድድር ለመሳተፍ ደግሞ አዲሶቹ ኢንተርናሽናል ዳኞች ዋና ዳኛ ሃይማኖት አዳነ ፣ ዋና ዳኛ ሄኖክ አበበ ፣ ረዳት ዳኛ ዘመኑ ሲሣይነውን ጨምሮ ባለ ልምዱ ረዳት ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ስምንት ሀገራትን በሚያሳትፈው ውድድር
በምድብ አንድ
ኤስቶኒያ (Estonia) – አውሮፓ
ግሬናዳ (Grenada) – ሰሜን አሜሪካ
ኬንያ (Kenya) – አፍሪካ
ሩዋንዳ (Rwanda) – አፍሪካ (አስተናጋጅ)
ምድብ ሁለት
አሩባ (Aruba) – ሰሜን አሜሪካ
ሊክተንስታይን (Liechtenstein) – አውሮፓ
ማካው (Macau) – እስያ
ታንዛኒያ (Tanzania) – አፍሪካ

