ኢትዮ ኤሌክትሪክ 0-5 ሲዳማ ቡና
38′ በረከት አዲሱ 54′ ፍፁም ተፈሪ 73′ ዘነበ ከበደ 77′ 90+2′ አዲስ ግደይ
ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በሲዳማ ቡና 5-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ጎልልል!!!! ሲዳማ ቡና
አዲስ ግደይ ከበረከት የተሻገረለችን ኳስ ተጠቅሞ 5ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
80′ ጨዋታው በሲዳማ ቡና ሙሉ የበላይነት ቀጥሏል፡፡ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ላለመውረድ የሚጫወት ቡድን ሳይሆን በሰንጠረዡ ወገብ የሚገኝ ቡድን እንቅስቃሴ ይመስላል፡፡ በተጫዋቾቹ ላይም የጨዋታ ፍላጎት አይታይም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
79′ ወሰኑ ማዜ ወጥቶ ፀጋዬ ባልቻ ገብቷል፡፡
ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና
77′ አዲስ ግደይ በድጋሚ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ በዚህኛው ስህተት አልሰራም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
76′ ኤሪክ ሙራንዳ ወጥቶ አዲስአለም ደበበ ገብቷል፡፡
74′ አዲስ ግደይ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ቺፕ ያደረገውን ኳስ ገመቹ አድኖታል፡፡
ጎልልል !!! ሲዳማ ቡና
73′ ዘነበ ከበደ አክርሮ የመታው ቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ ከመረብ አርፏል፡፡
ቀይ ካርድ
72′ ተስፋዬ መላኩ በአዲስ ግደይ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
66′ ማናዬ ፋንቱ ወጥቶ ዋለልኝ ገብሬ ገብቷል፡፡
62′ ማንኮ ያሻገረውን ኳስ ሀብታሙ መንገሻ በጭንቅላቱ ገጭቶ ቢሞክርም ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
57′ ብሩክ አየለ ወጥቶ አሸናፊ ሽብሩ ገብቷል፡፡
ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና
54′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ፍጹም ተፈሪ ሲመታው በተስፋዬ መላኩ ተጨርፎ ጎል ሆኗል፡፡
46′ ሙራንዳ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ በረከት መትቶ የግቡ ቋሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
የእረፍት ሰአት ለውጥ
ፒተር ኑዋዲኬ ወጥቶ ሀብታሙ መንገሻ ገብቷል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በሲዳማ ቡና መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
45′ የመጀመሪያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!! ሲዳማ ቡና
38′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ተጠቅሞ በረከት አዲሱ ከመረብ አሳርፏል፡፡
37′ አዲስ ግደይ የሞከረውን ኳስ ገመቹ በቀለ አውጥቶታል፡፡
35′ ጨዋታው ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ቅብብሎችም ቶሎ ቶሎ ይቋረጣሉ፡፡
29′ ከበረከት የተሻገረውን ኳስ ሙራንዳ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና
21′ አንተነህ ተስፋዬ (ጉዳት) ወጥቶ ተመስገን ካስትሮ ገብቷል፡፡
15′ በረከት አዲሱ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ሲዳማዎች ወደ ግብ በመድረስ የተሻሉ ቢሆኑም ጎል ፊት ስል መሆን አልቻሉም፡፡
** ሁለቱም ክለቦች ዋና አሰልጣኞቻቸውን ሳይዙ ገብተዋል፡፡ ኤሌክትሪክ በኤርሚያስ ተፈሪ ሲመራ ሲዳማ ቡና አለማየሁ አባይነህ እየተመራ ይገኛል፡፡
9′ በጥሩ ሂደት የመጣውን ኳስ በረከት አዲሱ ስቶታል፡፡ ወርቃማ የማግባት አጋጣሚ ነበር፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በሲዳማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡
የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰላለፍ
1 ገመቹ በቀለ
2 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 3 አልሳዲቅ አልማሂ – 15 ተስፋዬ መላኩ
23 ማናዬ ፋንቱ – 4 ማንኮ ክዌሳ – 9 አዲስ ነጋሽ – 10 ብሩክ አየለ
16 ፍፁም ገብረማርያም – 28 ፒተር ኑዋድኬ
ተጠባባቂዎች
22 አሰግድ አክሊሉ
5 አህመድ ሰኢድ
14 አማረ በቀለ
7 አለምነህ ግርማ
25 አሸናፊ ሽብሩ
24 ዋለልኝ ገብሬ
12 ሀብታሙ መንገሻ
የሲዳማ ቡና አሰላለፍ
1 ፍቅሩ ወዴሳ
2 ዘነበ ከበደ – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 33 አወል አብደላ – 15 ሳውሬል ኦልሪሽ
ወሰኑ ማዜ – 5 ፍፁም ተፈሪ – 20 ሙሉአለም መስፍን – 14 አዲስ ግደይ
9 በረከት አዲሱ – 13 ኤሪክ ሙራንዳ
ተጠባባቂዎች
89 አዱኛ ፀጋዬ
16 እምሻው ካሱ
6 አዲስአለም ደበበ
19 ተመስገን ካስትሮ
25 ክፍሌ ኪአ
27 ላኪ ባሪለዱም ሳኒ
11 ፀጋዬ ባልቻ