ትውልደ ኢትዮጵያዊው በኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል።
የስዊድኑ ጁርጋርደን ከቼልሲ ጋር ባደረገት የኮንፈረንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ይስሀቅ ሙልጌታ ግብ አስቆጥሯል።
ከኢትዮጵያዊው አባቱ እና ከኤልሳልቫዶራዊት እናቱ የተገኘው የአስራ ስምንት ዓመቱ አማካይ በሁለት እጋጥሚዎች ወደ ፌይኖርድ ወጣት ቡድን እና እስቶኮልም ካደረጋቸው የውሰት ቆይታዎች ውጭ ላለፈት ዓመታት እናት ክለቡን በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች ያገለገለ ሲሆን በኮንፈረንስ ሊግም የዛሬው ወሳኝ ጨዋታ ጨምሮ በሦስት መርሐ-ግብሮች ቡድኑን አግልግሏል። ከጁርጋርደን ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ ገና በለጋ ዕድሜው ለዋናው ቡድን በመጫወት የጀመረው ይህ አማካይ ከ2022 ጀምሮ በዋናው ቡድን ደረጃ መጫወት የጀመረ ሲሆን ከእናት ክለቡ ጋርም እስከ 2025 የሚያቆየውን ውል አለው።
ከጥቂት ዓመታት በፊትም በዚህ ሰአት በሌላው የስዊድን ክለብ ‘GAIS’ በመጫውት ላይ ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሀሩን ኢብራሂም ከኖርዌዬ ሞልደ ጋር በአውሮፓ ቻምፕዮንስ ሊግ መሳተፉ ይታወሳል።
