ቻምፕዮኖቹ ተከላካይ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል

ቻምፕዮኖቹ ተከላካይ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል

ኢትዮጵያ መድኖች ጋናዊውን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

በቅርቡ በካፍ ቻምፕዮንስ ሊግ ከዛንዚባሩ ምላንዴጌ የሚጫወተው ኢትዮጵያ መድን ከቡድኑ በተለያዩ ነባር ተጫዋቾች ምትክ ቀደም ብሎ ብሩክ ሙልጌታ እና ሙሴ ኪሮስን ማስፈረሙ ይታወሳል አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ የነበረው ጋናዊው የመሐል ተከላካይ ኢስማዒል አብዱልጋኒዮ የግሉ ለማድረግ ከስምምነት ደርሷል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የብርቱካናማዎቹ ቆይታው በ29 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2583′ ደቂቃዎች ቡድኑን በማገልገል 2 ግቦችን ያስቆጠረው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች ዋ ኦል ስታርስ ፣ ካሬላ ዩናይትድ እና አሻንቲ ኮቶኮ እንዲሁም ለኢራቁ ክለብ አልታላባ እና ለኮንጎው ቲፒ ማዜንቤ መጫወቱም ይታወሳል። አሁን ደግሞ በቀጣይ ውድድር ዓመት በአህጉራዊ መድረክ ተሳታፊ ለሆኑት በአሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ የሚመሩት ኢትዮጵያ መድኖች ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።