በጦና ንቦቹ ቤት ያለፉትን ሁለት ዓመት ቆይታ የነበረው አማካይ ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል።
በአሰልጣኝ ስዮም ከበደ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች ቡድናቸውን ለማጠናከር ስማቸው ከበርካታ ተጫዋቾች ጋር ተያይዞ የተነሳ ሲሆን እስካሁን ከግብ ጠባቂው አላዘር ማርቆስ ጋር መስማማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ብዙዓየው ሰይፉን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።
አማካዩ እግር ኳስን በትውልድ ሀገሩ ሮቤ ከተማ ካደረገ በኋላ በመቀጠል በሀላባ ከተማ በ2014 ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ በአዲስ አበባ ከተማ በመጫወት ራሱን ካስተዋወቀ በኋላ በወልቂጤ ከተማ ቆይታ ሲያደርግ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በጦና ንቦቹ ቤት በማሳለፍ አሁን ማረፊያውን አዳማ ከተማ ለማድረግ ተስማምቷል።
በሌላ ዜና አዳማ ከተማ በቀጣዮቹ ቀናት ጠንከር ያሉ ዝውውሮችን እንደሚፈፅም ይጠበቃል።