ምዓም አናብስት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀመሩ

ምዓም አናብስት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀመሩ

በአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት የሚመሩት መቐለ 70 እንደርታዎች ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።

በዝውውር መስኮቱ ሱሌይማን ሐሚድ፣ መሐሪ አመሀ፣ አብዲ ዋበላ፣ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ፣ ብርሀኑ አዳሙ፣ ጊትጋት ኩት እና ፍፁም ዓለሙን ለማስፈረም ተስማምተው የኬኔዲ ገብረፃዲቕ፣ ዘረሰናይ ብርሀነ እና የአሸናፊ ሀፍቱን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም የተስማሙት መቐለ 70 እንደርታዎች በመቀመጫ ከተማቸው መቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።

ባለፉት ቀናት ታዳጊ ተጫዋቾችን በመመልመል የሰነበቱት መቐለ 70 እንደርታዎች ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚዎች፣ ውላቸውን ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች እና ታዳጊዎች በማካተት በመቐለ ዩኒቨርስቲ ስቴድየም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ቀደም ብለው ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማሙ ተጫዋቾች ስብስቡን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።