ሽረ ምድረ ገነቶች የነባር ተጫዋቾች ውል ማደሳቸውን ቀጥለዋል

ሽረ ምድረ ገነቶች የነባር ተጫዋቾች ውል ማደሳቸውን ቀጥለዋል

አስር ታዳጊዎች ከእናት ክለባቸው ጋር ለመቀጠል ውላቸውን አራዝመዋል።

ቀደም ብለው የብሩክ ሐድሽ፣ ዋልታ ዓንደይ፣ ክፍሎም ገብረህይወት፣ ክብሮም ብርሀነ፣ ኬቨን አርጉዲ እና ጎይትኦም ነጋን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ያራዘሙት ሽረ ምድረ ገነቶች አሁን ደግሞ በ2017 የውድድር ዓመት ከታዳጊ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን አድገው ከቡድኑ ጋር ቆይታ ያደረጉትን ተከላካዮቹ አቤል ብርሀነ፣ ሰለሞን ገብረክርስቶስ፣ ፍርያት ጣሰው ፤ አማካዮቹ አቤል መዝገበ፣ ፀጋይ ፀሐዬ እና አማኑኤል ስንቀይ እንዲሁም የፊት መስመር ተጫዋቾች የሆኑት ሔኖክ ተወልደ፣ ዳንኤል ክፍሎም፣ ዓወት በሪሁ እና ሙሴ ዕቋር ከአሳደጊ ክለባቸው ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።