ወላይታ ድቻ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ

ወላይታ ድቻ ከካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውጪ ሆነ

በቶታል ኢነርጂስ ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ዙር የመልስ ጨዋታ ወላይታ ድቻ በሊቢያው አል ኢቲሀድ ትሪፖሊ ሽንፈት አስተናግዶ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት የመጀመርያ ጨዋታ ያለ ግብ ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አል ኢቲሀድ ትሪፖሊ 3-1 ማሸነፍ ችሏል።

በመጀመርያው አጋማሽ 18ኛው ደቂቃ ላይ ባለሜዳዎቹ በቴቴ ጎል ቀዳሚ መሆን ሲችሉ በአጋማሹ መገባደጃ ቴዎድሮስ ታፈሰ ድቻን አቻ በማድረግ የቡድኑን የማለፍ ተስፋ አለምልሞ ወደ እረፍት አምርተው ነበር።

ከእረፍት በኋላ ጠንክረው የቀረቡት ኢቲሀዶች ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፋቸውን ጎሎች በ72ኛው ደቂቃ በኖፌል አል ዛርሁኒ እና በ90ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በገባው አል ባይዚ አማካኝነት አስቆጥረው በድምር ውጤት 3-1 አሸናፊነት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።