የግብ ዘቡ አቡበከር ኑረ ምን አጋጠመው

የግብ ዘቡ አቡበከር ኑረ ምን አጋጠመው

ኢትዮጵያ መድን በድምር ውጤት ወደ ቀጣዮ ዙር ማለፉን ባረጋገጠበት ጨዋታ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ጉዳት አስተናግዷል።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ባለቤቱ ኢትዮጵያ መድን የመጀመሪያው ዙር የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታን በደርሶ መልስ ድምር ውጤት ምላንዴግን 4-3 በማሸነፍ
ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጨዋታ ማለፉን ማረጋገጡ ይታወሳል።

በዚህ ጨዋታ ወቅት በመጀመርያው አጋማሽ የወቅቱ የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ ባጋጠመው ጉዳት ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል ማምራቱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አቡበከር አሁን ያለበትን ሁኔታ እና የጉዳቱ መጠን ምን እንደሆነ ባደረግነው ማጣራት እግሩ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው እና የጉዳቱ መጠን ለሁለት ሳምንት ዕረፍት እንደሚያስፈልገው ሰምተናል።

የአቡበከር መጎዳቱን ተከትሎ በቀጣዮቹ ሳምንታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ ለክለቡ አገልግሎት የማይሰጥ ይሆናል። ኢትዮጵያ መድኖች ነገ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለሱም አውቀናል።