የጦና ንቦቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

የጦና ንቦቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

ያለፉትን ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ ያደረገው የመስመር አጥቂ መዳረሻው ወላይታ ድቻ ሊሆን ተቃርቧል።

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች ከሰሞኑ ከአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመርያው ዙር የማጣሪያ ውድድር ውጭ መሆናቸው ይታወቃል። አሁን ሙሉ ትኩረታቸውን ለሀገር ውስጥ ውድድር ያደረጉት የጦና ንቦቹ የመስመር አጥቂውን ብሩክ ኤልያስን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ከዚህ ቀደም በደቡብ ፖሊስ ፣ ሀምበርቾ እና ያለፉትን አራት ዓመታት በሀዋሳ ከተማ በመስመር አጥቂነት ያገለገለው ብሩክ ከወላይታ ድቻ ጋር በቅድመ ውድድር ዝግጅት አብሮ ሲሰራ ከቆየ በኋላ አሁን ፊርማውን ለማኖር ከስምምነት መድረሱን አውቀናል።