ወደ ላይቤሪያ አቅንተው የነበሩት አሰልጣኝ ውበቱ በሥራቸው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

የቀድሞ የዋልያዎቹ አለቃ እና በሀገሪቱ የተለያዩ ክለቦች ያሰለጠኑት ውበቱ አባተ ባሳለፍነው ዓመት ከፋሲል ከነማ ጋር ከነበራቸው ቆይታ በስምምነት ከተለያዩ በኋላ ለጥቂት ወራት ያለ ክለብ ቆይተው በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ላይቤሪያ የሚገኝ ክለብ የአሰልጥነን ጥያቄ ተቀብለው ማምራታቸው የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን ከያዙት ቡድን ‘Liberian International Shipping & Corporate Registry’ ‘Liscr’ ጋር ከአንድ ወር በላይ ሳይዘልቁ ለመለያየት መቃረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ ስለሆንን የአሰልጣኙን እና የክለቡን ጉዳይ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ እና ሰበታ ከተማን በውጭ ሀገርም የሱዳኑን አልአህሊ ሸንዲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡

